ደ
ሴ የካቲት 13/2017 (ኢዜአ)፡- የመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ግልጽ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የግዥ አሰራር መፍጠሩን የፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ ተናገሩ።
ባለስልጣኑ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በመንግስት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት አጠቃቀምና አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሰረት መስቀሌ፤ የግዥ ስርዓቱን ዲጅታላይዝድ በማድረግ ፈጣን፣ ግልጽና ፍትሃዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።፡
ለዚህም በፌዴራል የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
በአሰራሩ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት ግልጽ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የግዥ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር)፤ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓቱ የሀገርን በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲሁም ለመንግስታዊ አሰራር ግልጸኝነትና ለንግዱ ማህበረሰብ ጭምር የላቀ ሚና ያለው መሆኑን አንስተዋል።
የግዥ ስርአቱ በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የግዥ ስርዓት ከብዙ ውስብስብ ችግሮች ያስወጣ ስለመሆኑም ገልጸዋል።
በመሆኑም በአቅራቢ ነጋዴዎች ወደ ሲስተሙ በመግባት ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን መዘጋጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በስልጠናው በርካታ ነጋዴዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የግዥ ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025