አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- በ3ኛው ዙር የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ይፈፀማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለፁ።
3ኛው ዙር ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የ2017 ኤክስፖ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በመርሐ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት ብትሆንም የምርታማነት ታሪኳ ግን አዝጋሚ ነበር።
ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና ለምታደርገው ጉዞ መፋጠን የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መጀመሩን ገልፀዋል።
ንቅናቄው ባለፉት ሁለት ዓመታት ዘርፉ አጋጥመውት የነበሩ ችግሮችን በመፍታት በርካታ ስኬቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
በተለይም የሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት መቻሉንም አንስተዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ብቻ ሁለት ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉን በመግለጽ።
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፋ አጠቃላይ ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ያለው ድርሻ በየጊዜው እያደገ መምጣቱንም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ባለፋት ሁለት ዓመታት በተደረጉ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖዎች በፌዴራል ደረጃ ከ307 በላይ ኢንዱስትሪዎች መሳተፋቸውንና በአጠቃላይ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈፀሙንም ጠቅሰዋል።
ከሚያዝያ 29 እስከ ግንቦት 5 ቀን 2017 በሚካሄደው 3ኛው ዙር የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ይፈፀማል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
ከሀገር ውስጥና ከውጭ በርካታ የንግድ ስምምነቶችና የገበያ ትስስሮች ይፈጠራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ሚኒስትሩ አንስተዋል።
መንግስት በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የህግ ማዕቀፎችን ከማሻሻል ባለፈ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ተወካዮች በበኩላቸው ንቅናቄው አምራችና ሸማቹን በቀላሉ በማገናኘት ለዘርፉ መነቃቃት ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉ በተግባር ያስመሰከረ መሆኑን አንስተዋል።
ንቅናቄው በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ የነበረውን የተዛባ አመለካከት የቀየረ መሆኑንም የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ገልጸዋል።
3ኛው ዙር የኢትዮጵያ ታምርት የ2017 ኤክስፖ ላይ ከ200ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይሳተፉሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025