የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን ዕድሜና የቀድሞ ስልጣኔ የሚመጥኑ ናቸው - ሚኒስትር መላኩ አለበል

Feb 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን ዕድሜና የቀድሞ ስልጣኔ የሚመጥኑ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ መላኩ አለበል ገለፁ።

አቶ መላኩ አለበል እና በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ መሐመድ ሁሴን በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ሚኒስትር መላኩ አለበል በመስክ ምልከታው ወቅት እንደገለፁት በሀረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን የቀድሞ ዕድሜ እና ስልጣኔ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

ሀረር ከተቆረቆረች ከ 1,000 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረች ታሪካዊ ከተማ ብትሆንም በከተማዋ የነበረው ልማት የቀድሞ ስልጣኔና ዕድሜዋን የሚመጥን እንዳልነበር ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ታሪካዊና የስልጣኔ ፈር ቀዳጅ ከተማነቷ የምትጠቀሰው ሀረር ላይ በአሁኑ ሰዓት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች እና የተመዘገቡ ውጤቶች የአመራሩ ቁርጠኝነትን ያሳየ ነው ብለዋል።

በተለይ ከተማዋን ጽዱ፣ አረንጓዴና ውብ በማድረግ ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ጥራት እና ፍጥነትን መሰረት አድርገው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን የቀድሞ ምልከታ የቀየረ ሆኖ እንዳገኙት ገልፀዋል።

ሀረር አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ጨምሮ ሌሎች በርካታ ቅርሶችን በጉያዋ ያቀፈች በአገሪቱ ከሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ መሆኗን ጠቅሰው በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከተማዋን ምቹ እና ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ያደረጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ጁገል ህያው ቅርስ መሆኗን በመጠቆም በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የተከናወነው የመልሶ ልማት ስራ አካባቢውን ለነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ምቹ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።

በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ባጠቃላይ ተስፋ ሰጪና አበረታች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ በተለይ የቱሪዝም ዘርፉን ይበልጥ በማነቃቃት አበርክቶው የጎላ መሆን አክለዋል።

ሚኒስትሩ በሌላ በኩል በከተማው የኢንዱስትሪ እና የኢንቨስትመንት ስራዎችን ተዘዋውር የተመለከቱ ሲሆን ዘርፉ የተሻለ መነቃቃት የታየበት መሆኑን መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

አቶ መሐመድ ሁሴን በበኩላቸው በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በተሞክሮነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

በተለይ በአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ዙሪያ በ 1 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት ላይ በራስ አቅም ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ ፕሮጀክት ጥሩ ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን አክለዋል።

በከተማው ካሁን ቀደም በተገነባው የኑር ፕላዛ ውብ የማረፊያ ስፍራዎችን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ሰፋፊ እና ምቹ የእግረኛ፣ የተሽከርካሪ እና የብስክሌት መንገዶች የተገነቡበት፤በዘመናዊ እና የተዋቡ የመንገድ ላይ መብራቶች እና አረንጓዴ ልማትን በመፍጠር ምቹ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያስቻሉ መሆናቸውንም መመልከታቸውን ገልፀዋል።

ስራ አስፈፃሚዎቹ በነገው ዕለት ህዝባዊ ኮንፍረንሱን ይመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በጉብኝቱ ላይም በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ፅጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመር፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025