ሚዛን አማን፣ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፦ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ውይይት በሚዛን አማን ከተማ ተካሄዷል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ሊቀጠበብት ቀለመወርቅ አጥናፉ እና አቶ ሸንቃ ጋኪናንስ እንዳሉት በለውጡ መንግስት በግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ተጠቃሚ ሆነዋል።
ፓርቲው ቀረጾ የተገበራቸው ሃሳቦች የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያበስሩ እንደሆኑም ገልጸዋል።
የሚዛን አማን አየር ማረፊያን ለአብነት ጠቅሰው፤ ፕሮጀክቱ በጊዜ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ጥረቱ እንዲጠናከር አመልክተዋል።
አቶ ደምሴ ዶንታና መምህር ከድር ብርሃኑ በንጹህ መጠጥ ውሃ፣ በጤና አገልግሎት እና በመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማሻሻል የተጀመሩ ጥረቶች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል።
የመንግስትን የልማት ሥራዎች ስኬታማነትም የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ነዋሪዎቹ አረጋግጠዋል።
ውይይቱን የመሩት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ እንዳሉት መንግስት ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።
ትምህርትና ጤናን ጨምሮ ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የማህበራዊ ዘርፍ የልማት ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።
በፓርቲው የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ መሐመድ አሕመድ በበኩላቸው የተነሱ ሕዝብ ጥያቄዎችን በእቅድ ለመመለስ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025