ድሬዳዋ፣ የካቲት 17/2017(ኢዜአ) ፡-በድሬዳዋ የኮሪደር ልማት የስራ ባህልን ከመቀየር በዘለለ ድሬዳዋን ምቹና ተስማሚ የስራና የመኖሪያ ስፍራ የሚያደርግ መሆኑን ከንቲባ ከድር ጁሃር ተናገሩ።
በከንቲባ ከድር ጁሃር የተመራው የካቢኔ አባላት እየተገባደደ የሚገኘውን የ11 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት እየተመለከቱ ነው።
የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር በጉብኝታቸው ወቅት ከኮሪደር ልማቱ ፕሮጀክት ተቋራጮች ጋር የተወያዩ ሲሆን ልማቱን ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት ማጠናቀቅ የሚያስችል አቅጣጫን አስቀምጠዋል።
እንደ ከንቲባ ከድር ገለፃ ቀንና ማታ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የድሬዳዋን የስራ ባህል በከፍተኛ ደረጃ እየለወጠው ነው።
በተጨማሪም ድሬዳዋን ፅዱና ውብ የስራና የመኖሪያ መዳረሻ እንደሚያደርግ ጠቅሰው፤ በልማቱ ሂደት ተቀናጅቶ መስራት ያለውን ውጤት በሌሎች ፕሮጀክቶች ለመድገም እንደተሞኮሮ ተወስዷል ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክርቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው አስተዳደሩ የኮሪደር ልማትን ሆነ ሌሎች ፕሮጀክቶችን በጥራት፣ በፍጥነትና በተመደበለት በጀት አጠናቆ ለህብረተሰብ ለማስረከብ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ መሠረታዊ ልምድ የተቀሰመበት ወሳኝ ስራ መሆኑን በማስታወስ ።
የኮሪደር ልማቱ የነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚመልስ መሆኑን ጠቅሰው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ ዕድል አግኝተው ክህሎት እየቀሰሙ መሆናቸውን አንስተዋል።
የካቢኔ አባላቱም ቀሪ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በተቀናጀ መንገድ ዳር ለማድረስ የሚያደርጉትን ድጋፍና ክትትል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025