የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ፓርቲው የዜጎችን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ

Feb 25, 2025

IDOPRESS

ሆሳዕና፤ የካቲት 17/2017(ኢዜአ)፡- ብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሚኒስትር ፍቃዱ ተሰማ ገለጹ።

በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ህዝባዊ ኮንፍረንስ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

በብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሚኒስትር ፍቃዱ ተሰማ በኮንፍረንሱ ላይ እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲው እንደሀገር የዜጎችን የመልማት ጥያቄዎች የሚመልሱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያሳልጡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን በማጠናከር ወደ ኢንዱስትሪው የሚደረገውን ሽግግር ለማፍጠን በትኩርት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ተግባራቱ ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በበኩላቸው ፓርቲው የመልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት አቅዶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ተግባራትም ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ምላሽ የሚሰጡ ሆነው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

በተለይም የወጣቶችን ፍልሰት ለመቅረፍ የስራ አማራጮችን ማስፋት ላይ የሚከናወኑ ተግባራት ትኩረት መስጠት ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ በከተማዋ በተቀናጀ መልኩ የተጀመሩ የህዝብ ጥያቄ የሚመልሱና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

የልማት እቅዶች ተስፋ የሚሰጥ ውጤት እንዲያሳዩ ነዋሪው እያደረገ ያለውን ተሳትፎ ሊያጠናክር እንደሚገባም አመልክተዋል።

ከውይይቱ ተሳታዎች መካከል አቶ ገብሬ ሉደጎ አሁን ላይ በከተማዋ እየተተገበሩ የሚገኙ ተስፋ የሚሰጡ የልማት ስራዎች እንዲጠናከሩ የሚጠበቅብንን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይገባናል ብለዋል፡፡

ከተማዋን ውብና ተመራጭ በሚያደርግ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ኮሪደር ልማትን ጨምሮ የአስፓልት መንገድና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

በከተማዋ የህዝብ ጥያቄ የሆኑ የልማት ስራዎችን ፈትሾ ከማከናወን ባለፈ ለቀጣይ ትውልድ ጭምር ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ተሻለ ሀቤቦ ናቸው።

የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድና የጎርፍ መውረጃዎች እንዲሁም የመዝናኛ ስፍራዎችን ለአብነት ጠቅሰው ከተማዋን ተመራጭ የሚያደርጉ የልማት ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025