
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሩዝ ሰብል የሚለማን የመሬት ሽፋን ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መድረሱን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራስ በቅ ለመሆን በሰጠችው ትኩረት አሁን ላይ በስንዴ ምርት ራሷን ችላለች።
በስንዴ ምርት የተገኘውን ስኬት ደግሞ እስከ 2018 ዓ.ም በሩዝ ምርት ለመድገም በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በሩዝ ሰብል የሚለማ መሬት ሽፋን ከነበረበት ከ200 እስከ 300 ሺህ ሄክታር ወደ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር በላይ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
የሩዝ ምርትና ምርታማነት በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ጠቅሰው፤ ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ ከጃፓን መንግስት ጋር በትብብር እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026