አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮ-ቴሌኮም ለኢንተርፕራይዝ ደንበኞች ስራቸውን የበለጠ ማቀላጠፍ የሚያስችሉ አዳዲስ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በሰጡት ማብራሪያ የኢንተርፕራይዝ ደንበኞች መጠቀም የሚፈልጉትን የቴሌኮም አገልግሎቶች ምንም አይነት መሰረተ ልማት መገንባት ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎች ይፋ ተደርገዋል ብለዋል።
የኢንተርፕራይዞች ውጤታማነት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
ይፋ ከተደረጉ አገልግሎቶች መካከል የእንስሳት ሀብትን በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ይገኝበታል።
ኢትዮ-ቴሌኮም ኢትዮጵያ ያላትን የእንስሳት ሀብት በአግባቡ በመለየት በትክክል መረጃ መያዝና መመዝገብ እንዲሁም መጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በዚህም አርብቶ አደሩ የእንስሳት ሀብቱን በመጠቀም የኢንሹራንስና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኝ በቴክኖሎጂ የታገዘ መፍትሔ ይዞ መምጣቱን አመልክተዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ለማረጋገጥ ኢንተርፕራይዞችን ብቁና ተወዳዳሪ ሊያደርጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ግድ መሆኑንም አንስተዋል።
ኢትዮ- ቴሌኮም የኔትወርክ ሽፋንና ተደራሽነቱን በመጠቀም የደህንነት፣ የህክምና፣ የኮንስትራክሽንና ተያያዥ አገልግሎት ለሚሰጡ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ያልተገደበ ፈጣን የድምፅና የምስል አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ቴክኖሎጂም ይፋ አድርገዋል።
ተቋሙ ባንኮችና ማክሮ ፋይናንሶች ምንም አይነት የቴሌኮም መሰረተ ልማት ሳያስፈልጋቸው በኢትዮ-ቴሌኮም መሰረተ ልማት ተጠቅመው አገልግሎታቸውን ማስፋት፣ ማስተዋወቅና ለህብረተሰቡ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን መፍትሔ ይዞ መምጣቱንም አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ትምህርት ቤቶች ከተማሪዎችና ከወላጆች እንዲሁም ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በቴክኖሎጂ በመታገዝ በቀላሉ ማገናኘት የሚያስችል አገልግሎትም ይፋ ሆኗል።
አትዮ-ቴሌኮም ኢንተርፕራይዞች በቴክኖሎጂ ታግዘው ደንበኞቻቸውን በቀላሉ ማግኘትና ግብረ መልስ ማግኘት የሚችሉበትን አገልግሎትም ነው ዛሬ ይፋ ያደረገው።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025