ሀዋሳ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- በሲዳማ ክልል የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት ለስኬት እንዲበቁ የምክር ቤቱ የድጋፍና ክትትል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ ገለጹ።
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ሲሆን የአስፈፃሚውን የስድስት ወራት አፈፃፀም መገምገም ጀምሯል።
የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፤ ሁሉም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያደርጓቸው ጥረቶች የምክር ቤቱ ክትትልና ድጋፍ ያልተለየ መሆኑን ገልጸዋል።
በግብርናው ዘርፍ በበጋ መስኖ ልማት በማህበር የተደራጁ ዜጎችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል ብለዋል።
በሌማት ትሩፋት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በሌሎች የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የቱሪዝም ዘርፎች በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ተስፋ ያላቸው መሆናቸውንም አፈ ጉባኤዋ አንስተዋል።
በመሆኑም በክልሉ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት ለስኬት እንዲበቁ የምክር ቤቱ ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በሁሉም ዘርፎች የተያዙ ዕቅዶች መሬት ወርደው የህዝብን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ የምክር ቤት አባላት የሚያደርጉ ክትትልና ቁጥጥር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ተቋማት ለይቶ ለማበረታታት የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ጉባዔው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025