ሰቆጣ፤ የካቲት 19/2017(ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት የፍራፍሬ ልማቱ ውጤት እየታየበት መሆኑን በብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ ገለጹ።
የብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በዝቋላ ወረዳ አካሂዷል።
የብልፅግና ፓርቲ የዋግ ኽምራ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ባይነሳኝ በግምገማው ላይ እንዳሉት በብሔረሰብ አስተዳደሩ በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት የውሃ አማራጭን በመጠቀም የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሮችን አኗኗር እየቀየሩ መጥተዋል።
በተለይም የዝቋላ አርሶ አደሮች የአካባቢን ስነ ምህዳር መሰረት ያደረጉ የፍራፍሬ ዝርያዎችን በማልማት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
የልማት ተሞክሮውን በዞኑ ለማስፋት በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።
በአስተዳደሩ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በበኩላቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከአዝርእት ልማት ጎን ለጎን ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በትኩረት እየተሰራ ነው።
በዞኑም በዘንድሮው ዓመት በመስኖ ከሚለማው 4ሺህ 524 ሄክታር መሬት ውስጥ 373 ሄክታሩ በቋሚ ፍራፍሬና አትክልት እየለማ መሆኑን ገልፀዋል።
በቆላማ ወረዳዎች በክላስተር የአትክልት ልማትን ለማስፋፋት 18ሺህ አርሶ አደሮች በቋሚ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዝቋላ ወረዳ የፅፅቃ ከተማ ነዋሪ ቄስ ሙሉዓለም በላይ በበኩላቸው የፅፅቃ ወንዝን በመጠቀም አንድ ሄክታር ማሳቸው ላይ ማንጎ፣ ሎሚ፣ ቡና፣ ጌሾና ሌሎች ቋሚ አትክልቶችን እያለሙ ይገኛሉ።
የፍራፍሬ ልማቱን ውጤታማ ለማድረግ መሬታቸው ጪንጫ በመሆኑ ከሌላ አካባቢ አፈር አምጥተው በመደልደል መስራታቸውን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ከተረጂነት ለመላቀቅ ብቸኛው አማራጭ ተግቶ መስራት ነው ያሉት ቄስ ሙሉዓለም ወጣቱ ከእርሳቸው ተሞክሮ በመውሰድ የአካባቢውን ፀጋ በማልማት ተጠቃሚነቱን እንዲያረጋግጥም መክረዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025