
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፡- የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መምጣቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ።
ዋና ዳይሬክተሯ በተቋሙ የሪፎርም ስራዎች፣ እየተገኙ ባሉ ውጤቶና ቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅና የመከላከል አቅምን ማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ የለውጥ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
ከለውጥ ስራዎቹ መካከል የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ መዋሉን አስታውሰዋል።
ኮምፒውተርን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ መውጣቱን ጠቅሰው፣ ይህም ወንጀልን የመከላከል ሀገራዊ አቅምን ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ከውጭ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎችን ከደህንነት አኳያ በአግባቡ ተፈትሸው ወደ ሀገር እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያብራሩት።
ከቁልፍ መሰረተ ልማት ተቋማት ጥበቃ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል የሚችሉበት አቅም እንዲገነቡ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የተሻለ የአሰራር ስርዓት እንዲኖራቸው አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።
የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በዘርፉ የሰው ሃይልን ለማፍራት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ለአብነትም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ታዳጊዎች በክረምት መርሃ ግብር እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026