አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የኤሌክትሮኒክ ግዢ ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ገለፁ።
የፌደራል የመንግስት ግዢ አገልግሎት የፌደራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ገምግሟል።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ድሪባ ኢቲቻ(ዶ/ር) እንዳሉት ኤሌክትሮኒክ ስርዓት መተግበሩ ግልፅነት እና ተጠያቂነትን በመፍጠር ለአገልግሎት አሰጣጡ ቀልጣፋ እንዲሆን አስችሏል ብለዋል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በወቅቱ ተልዕኮውን በውጤታማነት እንዲወጣ እያገዘ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ታድዮስ ሜንታ(ዶ/ር) በበኩላቸው የግዢ ስርዓት ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት ወጪ ቆጣቢና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ማስቻሉን ነው የጠቀሱት።
በዚህም ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለማከናወን በከፍተኛ ደረጃ እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።
የፌደራል የመንግስት ግዢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ አስማረ ይገዙ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት ለፌደራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በኤሌክትሮኒክ ግዢ (e-GP) መፈጸሙን ተናግረዋል።
በግማሽ አመቱ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በሽያጭ በማስወገድም ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገኘቱን ነው የተናገሩት።
የቴክኖሎጂ ግብዓትን በማሟላትና የአቅም ግንባታ ስራ በመሰራቱ የማዕቀፍ ስምምነትና ስትራቴጂያዊ ግዢዎችን ሙሉ በሙሉ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ግዢ ስርዓት ተፈጻሚ እንዲሆኑ መደረጉን ጨምረው ገልጸዋል።
ከተቋሙ የሪፎርም ስራዎች መካከል የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ዋነኛው ሲሆን ለውጤታማነቱ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል።
ቀደም ባሉ ጊዜያት ከሲስተም መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ከተገልጋዮች ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎች በአሁኑ ወቅት እንዲቀረፉ መደረጉን ጠቅሰዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025