ሀዋሳ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፡-የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ከ4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት፣ የተለያዩ ሹመቶችና አንድ አዋጅ በማጽደቅ ተጠናቀቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ሹመት የሰጠው ለሁለት የቢሮ ሃላፊዎችና ለ46 ዳኞች መሆኑም ተመላክቷል።
ምክር ቤቱ ለክልሉ የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ ከፌዴራል መንግስትና ከክልሉ መንግስት ገቢ በአጠቃላይ 4 ቢሊዮን 674 ሚሊዮን 134 ሺህ ብር በጀት አጽድቋል።
ከበጀቱ ውስጥ ከ2 ቢሊዮን 842 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ከፌዴራል መንግሥት የተገኘ ሲሆን ቀሪው ከክልሉ መንግሥት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
ምክር ቤቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አቅራቢነት ሹመት የሰጠው ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ እና ለገቢዎች ቢሮ ሥራ ሀላፊዎች ነው።
በዚህም አቶ ሀይሌ አርሲሳ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም አቶ ደምሴ እሳቱ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል።
በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቅራቢነት በክልሉ ለሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችም 46 ዳኞችን ምክር ቤቱ ዛሬ ሹመት ሰጥቷል።
ለዳኝነት ሹመት ከተሰጣቸውም አራቱ ሴቶች ናቸው።
ዳኞቹ ለህብረተሰቡ ትክክለኛና ሚዛናዊ ፍትህ በመስጠት በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግሉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ደምሴ ዱለቻ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሁለት ዳኞችን በስነምግባር ጥሰት ምክንያት ከሃላፊነታቸው ያሰናበተ መሆኑን ገልጸው፣ ሌሎች 34 ዳኞች እያንዳንዳቸው የሦስት ወር ደመወዝ መቀጣታቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ ከሀላፊነት የተነሱ አስፈጻሚ አካላት፣ የህዝብ ተመራጮች እና የዳኝነት አካላት መብትና ጥቅማ ጥቅሞችን ለመወሰን የወጣ አዋጅና አንድ ደንብ በማጽደቅ ተጠናቋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025