
ደሴ ፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፡- በደሴ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ለህዝብ የተገባውን ቃል በተግባር የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከደሴ የተወከሉት የፓርላማ አባልና የደሴ ከተማ ምክር ቤት አባላት፣ ከነዋሪዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተለይም በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማድነቅ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በደሴ ከተማ አስተዳደር የተገነቡት የመሰረተ ልማት አውታሮች መንግስት ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር ያረጋገጡ ናቸው።
ከውይይት ተሳታፊዎች መካከል አቶ አህመድ ዓሊ፤ በከተማዋ ቀደም ሲል ይሰሩ የነበሩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከመጓተትም ባለፈ የጥራት መጓደል የሚስተዋልባቸው እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በዚህም ለህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ሆነው መቆየታቸውን አንስተው አሁን ላይ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች ግን በጥራት፣ በፍጥነትና የሰዎችን ተጠቃሚነት መሰረት ያደረጉ ስለመሆናቸው አንስተዋል።
መንግስት ለህዝቡ በገባው ቃል መሰረት ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ተናግረው እኛም የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።
የልማት ስራው እንቅስቃሴ በጥሩ ጎኑ ቢነሳም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች ግን ውለው ሳያድሩ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።
ሌላው የምክክሩ ተሳታፊ አቶ መላኩ አራጌ፤ የደሴ መናኸሪያ ግንባታን ጨምሮ የመንገድ፣ የካናልና ሌሎችም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በማንሳት ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።
የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት በማፅናት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማሳካት የሁላችንም እገዛና ትብብር ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አገሪቱ እንድሪስ፤ በከተማዋ ለሚከናወኑ ስራዎች መሳካት ለአስፈጻሚው አካል የተጠናከረ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ ረገድ የከተማው ነዋሪ ድጋፍና እገዛ በማድረግ ጭምር የልማቱ አጋር መሆኑም ተጨማሪ አቅም ሆኖናል ነው ያሉት።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የደሴ ከተማ ተወካይ የሆኑት ማህተም ኃይሌ(ዶ/ር)፤ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ህብረተሰቡን በልማትና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን በተግባር ተመልክተናል ብለዋል።
ይህም የህዝቡና በየደረጃው ያለው አመራር ትብብርና ለልማት የጋራ አላማ ሰንቆ በመሰራቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም የሰላም ጉዳይ የሁሉም ነገሮች መሰረት መሆኑን አንስተው ሰላምን በማስጠበቅ ልማትን ማጠናቀቅ የሁል ጊዜም ዓላማ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
በዚህ ረገድ የከተማው ምክር ቤት ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይነት የሁላችንም ሚና ይታከልበታል ሲሉ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የደሴ ከተማ ምክር ቤት አባላትና ሌሎችም ተሳትፈዋል፡፡
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026