በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች በተለያዩ አማራጮች ከተረጂነትና ጥገኝነት ተላቀው ራሳቸውን ለመቻል፣ ሕይወታቸውን ለመቀየርና ኑሯቸውን ለማሻሻል እየጣሩ ይገኛሉ።
ከነዚህም መካከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በልማት ማህበር የተደራጁ የሴት አደረጃጀቶች እና በድሬዳዋ አስተዳደር በሴፍትኔተ መርሕ ግብር የታቀፉ አርሶ አደሮች ይገኙበታል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በልማት ማህበር ተደራጅተው በገቢ ማስገኛ ሥራ የተሰማሩ ሴቶች ከጠባቂነት ወጥተው ተጠቃሚ እየሆኑና የሥራ ባህላቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን ይገልጻሉ።
በዞኑ ወናጎ ወረዳ 50 እናቶችን ይዞ የተደራጀው የሃንጅኔ ልማት ማህበር ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከ5 ሺህ በላይ ዶሮዎችን ለአባላቱና ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት ለሌማት ትሩፋት ስኬታማነት የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው።
የማህበሩ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘርጌ መላቱ እንደሚሉት፣ ማህበራቸው በቀን የ45 ቀን የዶሮ ጫጩቶችንም ለገበያ እያቀረበ ሲሆን ከሚያቀርቧቸው ዶሮዎች ሽያጭ በአንድ ዙር ከ30 ሺህ ብር በላይ ትርፍ እያገኙ ነው።
በማህበር ተደራጅተው በመስራት ከጠባቂነት ተላቀው በኢኮኖሚ ራስን ለመቻል እየጣሩ ሲሆን ለማህበሩ አባላት በብድር ማቅረቡ በዶሮ እርባታ ተጨማሪ ሥራና ገቢ እንዲያገኙ ማስቻሉን ገልጸዋል።
በዞኑ ዲላ ዙሪያ ወረዳ የቁንስኔ ራኮ ፉሎ ማህበር ሰብሳቢ ወይዘሮ አስናቀች ጂክሶ በበኩላቸው ቆጮን እሴት ጨምረው ለገበያ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የታጠበና የደረቀ ቆጮ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋት የበኩሉን ሲሰራ መቆየቱ ጠቅሰዋል።
በዚህም እሳቸውን ጨምሮ የማህበሩ አባላት ከጠባቂነት ተላቀው ኑሯቸውን እያሻሻሉ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በማህበር ተደራጅተን መንቀሳቀሳችን ለሥራ ያለንን ትጋት አሳድጎታል ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ መዓዛ ደስታ ናቸው።
በዞኑ ከ190 ሺህ በላይ ሴቶች በልማት ማህበር ተደራጀተው በተለያዩ የገቢ ማስገኝ ሥራዎች መሰማረታቸውን ያነሱት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ሴቶችና ሕጻናት መምሪያ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ዘመናይ ህርባዬ ናቸው።
የቤት እመቤት የነበሩ ሴቶችን ከጠባቂነት በማውጣት የገቢ አቅማቸውንና የሥራ ባህላቸውን ለማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ዘላቂ የእሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ እዮብ ሳሊ እንዳሉት ደግሞ በጌዴኦ ዞን 5 ወረዳዎች ለተደራጁ ከ2ሺህ 500 በላይ እናቶች ከ610 ሺህ ብር በላይ መነሻ ካፒታል ድጋፍ ተደረጓል።
በ45 ቀን ጫጩት፣ በቆጮ ንግድ፣ በጓሮ አትክልትና በቃጫ ሥራ ተደራጅተው ወደሥራ እንዲገቡ መደረጉንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል በድሬዳዋ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ አምራችነት ባደረግነው የተቀናጀ ጥረት ውጤት እያገኘን የሚሉት የሴፍትኔት መርሐ ግብር ተጠቀሚዎች ናቸው።
በአስተዳደሩ ብየአዋሌና የዋሂል ገጠር ክላስተር አርሶአደሮች እንደሚሉት በቀበሌዎቻቸው በስፋት የተጀመሩት የተፋሰስ ልማት፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሃግብሮች ትግበራ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሻገር እያገዟቸው ነው።
አርሶ አደር አቶ ኡስማን መሐመድ እንዳሉት፤ በቀበሌያቸው የሚያገኙት የሴፍቲኔት እገዛ ከእርዳታ እንዲላቀቁና ሰርተው ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉ አድርጓቸዋል።
መንግስት እያደረገ የሚገኘው ድጋፍና ክትትል በአጭር ጊዜ ከእርዳታ ተላቀን ምርትና ምርታማነታችንን እንድናሳድግ አድርጎናል ብለዋል።
ሌላው አርሶአደር አሊሾ ሲዮ በበኩላቸው ሁሉም ነዋሪ ከልመናና ከእርዳታ ለመገላገል በቁርጠኝነት ተግቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
"እኔ ከማመርተው ድንች፣ ቲማቲምና ሽንኩርት በዓመት ከ100 ሺህ ብር በላይ ገቢ አገኛለሁ" ያሉት አርሶ አደሩ፤ በአሁን ሰዓት ከሴፍቲኔት እገዛም ነፃ ሆነው እስከ 200 ሺህ ብር ቆጥበዋል።
የገጠሩ ነዋሪ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ አሻራ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት መጀመሩ ከተረጂነት የመላቀቁን ጉዞ ፍሬያማ እያደረገለት ይገኛል ያሉት ደግሞ አርሶ አደር መሐመድ አህመድ ናቸው።
በአካባቢው ከሰሞኑ የስራ ጉብኝት ያደረጉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደሚሉት በገጠር ቀበሌዎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየተካሄዱ የሚገኙ ስራዎች አበረታች ናቸው።
በቀጣይም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025