የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በዩኒቨርሲቲው እየተገነባ ያለው የምርምር ፓርክ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ያፋጥናል - አቶ መላኩ አለበል

Mar 3, 2025

IDOPRESS

አዳማ፤ የካቲት 22/2017(ኢዜአ)፦ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እየተገነባ ያለው የምርምርና ቴክኖሎጂ ፓርክ የምርምር ሥርፀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን እንደሚያፋጥን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።

ዩኒቨርሲቲው ያስገነባቸውን የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዛሬ አስመርቋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ ዛሬ በዩኒቨርሲቲው ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች ለመማር ማስተማር ስራው አዎንታዊ ሚና አላቸው።

በተለይ በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የምርምርና የቴክኖሎጂ ፓርክና ዳታ ሴንተር የምርምር ሥርፀትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል።

እንደ ሀገር ኢንዱስትሪውን በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ አዳዲስ የአመራረት ሂደትን ለመከተልና ቴክኖሎጂን ለማላመድ ወሳኝ መሆናቸውንም ነው ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን ማስተዳደር እንዲችሉና ራስ ገዝ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።

ለዚህም አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለገቢ ማመንጫነት አስገንብቶ ዛሬ ካስመረቃቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውን የቢዝነስ ሴንተር በማሳያነት ጠቅሰዋል።

ምቹ የሥራ አካባቢ መፍጠርና የመምህራን መኖሪያ ቤት ችግርን መፍታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለውም አቶ ኮራ አስገንዘበዋል።

በተለይ የህፃናት ማቆያ በተደራጀ መልኩ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱ ሠራተኞች ሳይቸገሩ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ያስችላቸዋል ብለዋል።

አቶ ኮራ እንዳሉት በአዳማ ዩኒቨርሲቲ በግንባታ ላይ ያለው የምርምር ፓርኩ ተቋሙን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር የፈጠራና የምርምር ግኝቶች ወደ ውጤት እንዲቀየሩ የሚያደርግ ነው።

ይህም ሀገርን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ ወደፊት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች ምሳሌ መሆናቸውንም አቶ ኮራ ጠቅሰዋል።

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሚ ጉታ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት አምስት ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት እንዲሁም በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራና በሳይንስ ዘርፍ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በተለይ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶቹ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ልጆቹ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኙ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ዛሬ ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች ባለ አራት ወለል የቢዝነስ ማዕከል ህንፃ፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የህፃናት ማቆያ ማዕከል፣ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የመምህራንና የሠራተኞች የመዝናኛ ማዕከል ናቸው።

ከእነዚህ በተጨማሪ 14 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ፣ የአይሲቲ እና የዳታ ማዕከል፣ ሁለገብ የስብሰባ ማዕከልና ሕንጻዎች እንዲሁም የምርምርና የቴክኖሎጂ ፓርኩ በቅርቡ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025