ባህርዳር፤የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፦ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ክልላዊ የግብርና ምርምር ስራዎች አውደ ጥናት በባህርዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪና ግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፤ በሁሉም የግብርና ምርቶች ምርትና ምርታማነት ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን ገልጸዋል።
በክልሉ ምርታማነትን ይበልጥ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው መድረኩ ለዚህ ትልቅ ግብአት እንደሚሆንም ገልጸዋል።
የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስማረ ደጀን (ዶ/ር)፣ ኢንስቲትዩቱ የክልሉንና የሀገሪቱን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ቀናት በሚካሄደው የምርምር ስራዎች አውደ ጥናትም በርካታ የምርምር ስራዎች ቀርበው የሚገመገሙ መሆኑን ጠቁመዋል።
በምርምር የሚፈልቁ የሰብል፣ የእንስሳት፣ የመስኖ፣ የተፈጥሮ ሃብትና ሌሎችም ግኝቶች ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና የአካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ፕሮፌሰር መልካሙ አለማየሁ፤ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የምርመር ዘርፎች ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዓመታዊው የምርምር አውደጥናት ላይ በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025