አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፡-የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች በጃፓን ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው በ33ኛው የእስያ፤ አረብና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ጸጋ ለባለሀብቶች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎታቸውን አሳይተዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) መንግስት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለዉጭ ባለሀብቶች የበለጠ ቀልጣፋ፤ ሳቢ እና ተመራጭ ለማድረግ የወሰዳቸዉን የፖሊሲ ማበረታቻዎች፤ ሀገር በቀል የሪፎርም ስራዎችን በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ዉስጥ ያሉ የአንድ መስኮት አገልግሎቶችን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ኢትዮጵያ ሰፊ ወጣት የሰው ኃይል ያላት ሀገር መሆኗ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን አድርጓታል ሲሉ ገልጸዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸዉ የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና የነጻ ንግድ ቀጣና ዉስጥ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች መሟላታቸውን አመልክተዋል።
በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል በተመጣጣኝ ዋጋ ለኢንቨስተሮች መቅረቡ፣ ምቹ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ፣ሰፊ የገበያ እድል መኖሩ ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፍ ባለሃብቶች የበለጠ ተመራጭ መዳረሻ ያደርጋታል ብለዋል።
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ በበርካታ መመዘኛዎች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሀገር ሆናለች ሲሉ ተናግረዋል።
መንግስት ከዚህ ቀደም የኢንቨስትመንት ዘርፉ ዋነኛ ማነቆ የነበሩ ችግሮችን በመለየት የወሰዳቸዉ እርምጃዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በአጭር ጊዜ ለውጥ እያመጡ እንደሆነ መግለጻቸውን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025