ነገሌ ቦረና፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፡- በምሥራቅ ቦረና ዞን ከ158 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለበልግ አዝመራ መዘጋጀቱን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡
በምሥራቅ ቦረና ዞን ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የዝናብና የበልግ አዝመራ ወቅት መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ቦነያ ሁቃ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ በዘንድሮው ዓመት ከ158 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለበልግ አዝመራ የተዘጋጀ ሲሆን፤ እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴ 70 ሺህ 300 ሄክታር መሬት ለሶስተኛ ዙር ታርሶ ለዘር ተዘጋጅቷል፡፡
በዘንድሮው ዓመት ለበልግ አዝመራ የተዘጋጀው አጠቃላይ መሬት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ16 ሺህ 135 ሄክታር እንደሚበልጥም ተናግረዋል፡፡
ከዞኑ የበልግ አዝመራ ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ አጠቃላይ ምርት ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን በዞኑ ስምንት ወረዳዎች 41 ሺህ 427 አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የማሳ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
በጽህፈት ቤቱ የግብአት ስርጭትና አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ አብዱረሂም አብዱረህማን በበኩላቸው እስካሁን 13 ሺህ 580 ኩንታል ማዳበሪያ ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡
በዞኑ ስምንት ወረዳዎች ለዘንድሮ የበልግ አዝመራ ከ104 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተጨማሪም ከ28 ሺህ ኩንታል በላይ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የተባዛ የአከባቢው ዘር ማዘጋጀታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
የነገሌ ቦረና ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አቶ ብርቁ በላቸው የመኸሩ ዝናብ ቆይታ አጭር ስለነበር የጠበቁትን ያክል ምርት እንዳላገኙ ያስታውሳሉ፡፡
በመኸር አዝመራው የጎደለውን ምርት በተያዘው የበልግ እርሻ ለማካካስ ከአራት ሄክታር በላይ መሬት ደጋግመው በማረስ በጤፍ ዘር ለመሸፈን ተዘጋጅተዋል፡፡
ምርትና ምርታመነትን ለማሳደግም ስምንት ኩንታል የአከባቢ ዘርና የአፈር ማዳበሪያ አዘጋጅቻለሁ ብለዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025