አዲስ አበባ፤የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፦የገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ውጤታማነት ለማዋል የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የገጠር ትስስርን ከምግብ ዋስትና ፕሮግራም ትግበራ ጋር ለማሳለጥ በተዘጋጀው መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት መስጠት ጀምሯል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በዚሁ ወቅት፤ የገጠር መንገድ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማሳለጥ ለሚያስችሉ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የገጠር መንገድ ተደራሽነትን ለማስፋት በዓለም ባንክ ድጋፍ በክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉንም አውስተዋል።
በፕሮጀክቱም የአዳዲስ የመንገድ ግንባታዎች እና የገጠር መንገድ ጥገና ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹን በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ጠቁመው በተቻለ አቅም ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድሞ በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም ለማህበረሰቡ ምቹ የመንገድ ተደራሽነትን ለመፍጠር ብሎም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተገኙት የክልል ባለድርሻ አካላት ፕሮጀክቶቹን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ታደሰ ይርዳው የክልሉን ህዝብ የልማት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመንግስት በጀት ከሚሰሩ ልማቶች በተጨማሪ ከአጋር ድርጅቶች በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የትግራይ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሲሳይ አማረ በበኩላቸው በፕሮገራሙ ስምንት ወረዳዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ጠቅሰው፤ ከወረዳዎቹ መካከልም በዚህ አመት በሁለቱ ላይ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡
የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጅስቲክስ ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ሄለን ታምሩ እንዳሉት በፕሮግራሙ የሚገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጥራት ተሰርተው ለአገልግሎት እንዲበቁ ክትትል እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025