መቀሌ፤ የካቲት26/2017 (ኢዜአ) ፡-በትግራይ ክልል በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የታቀፉ ወገኖች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አልማዝ ገብረፃዲቅ ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ በአምስት ከተሞች የምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
በዚህም ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በልማታዊ ሴፍቲኔት በማቀፍ ሰርተው እንዲለወጡ የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።
በመጀመሪያው ዙር የከተሞች የምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በአምስት ከተሞች ከ34 ሺህ 600 በላይ ዜጎች መታቀፋቸውን አስታውሰው በግማሽ በጀት ዓመቱ ሰርተው ለሚከፈላቸውና በቀጥታ ለሚደገፉ ወገኖች ከፌደራል መንግስት የተላከ 14 ሚሊዮን ብር ስራ ላይ መዋሉን ገልፀዋል።
በሁለተኛው ዙር የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎችም ሰርተው በመለወጥ የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ከመርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎች መካከል በመቀሌ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ መሰረት ገብረ እግዚአብሔር፤ በወር ሰርተው ከሚከፈላቸው ወርሃዊ ደሞዝ 20 በመቶውን በመቆጠብ ህይወታቸውን በዘላቂነት ለማሻሻል ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
ሌላኛዋ የከተማው ነዋሪ ወጣት ዛይድ አለምሰገድ፤ በአረንጓዴ ልማት ላይ በመሰማራት በተለይ የተተከሉ ችግኞች እና የውበት ስፍራዎች በመንከባከብ በወር አምስት ሺህ ብር እንደምታገኝ ተናግራለች።
በመርሃ ግብሩ ሰርተን መለወጥ እንደምንችል ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ ለስኬት እየተጋን እንገኛለን ብላለች።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025