
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- መንግስት ሁሉን አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችሉ ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ፎዝያ አሚን(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር ለሴቶች እና ወጣቶች የዲጂታል ፋይናንሻል አገልግሎት ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀ እና የዲጂታል አቅምን ማጎልበት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ፎዝያ አሚን (ዶ/ር) መንግስት በኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የሴቶችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን እንደሚገባም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ አበክራ እየሰራች እንደምትገኝ ጠቅሰው ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አመልክተዋል።
ስልጠናው በዲጂታል ባንክ አገልግሎትና በዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት እድሎችና ተግዳሮቶች፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ የቴሌ ብር አገልግሎት ለሴቶች እና ሌሎች ተጓዳኝ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026