
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29 /2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ግምታቸው ከ939 ሚሊዮን ብር የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት ከየካቲት 21 እስከ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
በዚህም 573 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ እና 365 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች፤ በድምሩ 939 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መያዛቸውን ነው ያስታወቀው፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል የተለያዩ ማዕድናት፣ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል።
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ መሆናቸውን ገልጿል።
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ዘጠኝ ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና ሶስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ ንግድ ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ የበኩላቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026