ሆሳዕና፤ የካቲት 30/2017 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞችን ፅዱ፣ ውብና ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በሆሳዕና ከተማ ለኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ ከተሞችን ፅዱ፣ ውብ፣ ተወዳዳሪና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
በክልሉ ባሉ ሰባት የክላስተር ማዕከል ከተሞች ከ165 ኪሎ ሜትር በላይ የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፣ ልማቱ ከተሞችን ውብና ተወዳዳሪ ከማድረግ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል እየቀየረ መሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከተሞችን ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የሆሳዕና ከተማን ጨምሮ በሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራን ጨምሮ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎ መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ጡምደዶ በበኩላቸው፣ በከተማ አስተዳደሩና በህዝብ ተሳትፎ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ መሆኑንም አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የወጣቶች መዝናኛና ሌሎች ፕሮጀክቶች ከተማዋን ተወዳዳሪና ለኑሮ ተመራጭ የሚያደርጉ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አስተዳደሩ ልማቱ እንዲፋጠን የጀመረውን ጥረት ያጠናክራል ብለዋል፡፡
የልማት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብና ጥራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማዋል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ በልማቱ የህዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የሀድያ ዞን አመራሮች እንዲሁም ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025