አዳማ ፤መጋቢት 2/2017(ኢዜአ )፡- በአዳማ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ከ41 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን የከተማ አስተዳደሩ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የከተማዋ የስራ እድል ፈጠራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ጠይብ፤ በከተማዋ በስራ እድል ፈጠራ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት በተለያዩ መስኮች ለ31 ሺህ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።
በዚህም በግብርና፣ በወተት ልማት፣ በዶሮና በንብ ማነብ፣ በዓሳ እንዲሁም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለብዙዎች የስራ እድል መፈጠሩን አንስተዋል።
በግማሽ ዓመቱ ከ41 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረው በከተማዋ የዓሣ እርባታ ኩሬዎችና የንብ ማነቢያ ቀፎዎች ለወጣቶች መተላለፋቸውን ጠቅሰዋል።
እንዲሁም የወተት ላሞችና የዶሮ እርባታ ማዕከላት መገንባታቸውን ያነሱት ሀላፊው እንዲሁም የማምረቻ ማእከላት መሰራታቸውንም ገልፀዋል።
እኒሼቲቮቹን ውጤታማ ለማድረግ ከተማ አስተዳድሩ የውሃ፣ መብራትና የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ማሟላቱን ተናግረዋል።
ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር የፋይናንስ አቅርቦቱን ሟሟላት መቻሉንም ተናግረው በዚህም መሰረት 264 ሚሊዮን ብር ለ166 ማህበራት ብድር መሰጠት ተችሏል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025