የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በአማራ ክልል ለመሰብሰብ የታቀደውን ግብር ለማሳካት ሁሉን አቀፍ ጥረት ይደረጋል

Mar 12, 2025

IDOPRESS

ጎንደር፤መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል እየሰፈነ የመጣው ሰላም የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በቀሪ ወራት ለመሰብሰብ የታቀደውን ግብር ለማሳካት ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚደረግ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።


የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ ለገቢ ሰብሳቢ ሠራተኞች፣ለአጋር እና ባለድርሻ አካላት ያዘጋጀው የግብር ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።


በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ሃላፊው አቶ ክብረት መሃመድ እንደገለጹት፥ በአሁኑ ወቅት በክልሉ የሰፈነው ሰላም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ ለልማትና ለሰላም ሥራዎች ለማዋል የሚያስችል ነው።


በዚህም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ለክልሉ ገቢ አሰባሰብ ዕቅድ መሳካት በጋራ ሊረባረቡና ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።


በክልሉ በበጀት ዓመቱ 71 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብርና ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዶ ባለፋት ስምንት ወራት ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።


የተሰበሰበው ገቢም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለው ጠቁመው፣ በክልሉ እየተሻሻለ የመጣው ሰላም ለብልጫው አንድ ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።


በቀሪ ወራት ዕቅዱን ለማሳካት የአመራሩና የግብር ሰብሳቢ ባለሙያዎች የተቀናጀ ጥረትና ርብርብ ወሳኝ መሆኑንም አስታውቀዋል።


ግብር ለሀገር ልማትና እድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወትና ለህዝብም የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም ተናግረዋል።


የጎንደር ከተማ የልማት ጉዞ የሚፋጠነው ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ መሰብሰብ ሲቻል ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ናቸው።


በከተማው የልማት ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ያሉት በግብር በተሰበሰበ ገቢ መሆኑን ጠቁመው፣በየደረጃው ያለው አመራር ለግብር አሰባሰብ ሥራው ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።


የጎንደር ከተማ ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ጥሩዬ አታክልት በበኩላቸው፥በበጀት ዓመቱ በከተማው ከ3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን አውስተዋል።


ባለፋት ሰባት ወራት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ለልማትና ለሰላም ሥራዎች እንዲውል መደረጉንም ጠቁመዋል።


በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የከተማው የገቢ ሰብሳቢ ባለሙያዎችና አጋር አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025