የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ የመስኖ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ተግባር እየተከናወነ ነው

Mar 12, 2025

IDOPRESS

ባሕር ዳር፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ የመስኖ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ አየልኝ መሳፍንት ለኢዜአ እንዳሉት፤ አርሶ አደሩ ከዝናብ ጠባቂነት ተላቆ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ዓመቱን ሙሉ እንዲያለማ በዘመናዊ መስኖ ልማት ተጠቃሚ እየተደረገ ነው።

በተያዘው በጀት ዓመት ከ23 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚያስችሉ 154 መካከለኛና አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ታቅዶ 67 ፕሮጀክቶችን ወደ ግንባታ ማስገባት መቻሉን ጠ


ቅሰዋል።

ከነዚህም መካከል አራት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ልማት መግባታቸውን አንስተዋል።

ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ሲበቁ ከ53 ሽህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል።

ሌሎች 17 የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ከተቋራጮች ጋር ውል በመፈጸም መስጠቱን አመልክተው፤ የታቀደውን ለማሳካት ከወዲሁ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከነባሮቹ በተጨማሪ እየተከናወነ ያለው የመስኖ ፕሮጀክቶችን የማስፋፋት ተግባር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ቀጣይ ወደ ግንባታ የሚገቡ የ110 ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በክልሉ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመስኖ መልማት እንደሚችል ጠቅሰው፤ እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው 10 በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀሪውም ለማልማት ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጀክቶች የማስፋፋቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025