የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

አስተዳደሩ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎች የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገለፀ

Mar 15, 2025

IDOPRESS

ደብረ ብርሀን፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎች የድርሻውን እንደሚወጣ አስታውቋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የ2ኛ እና የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የጥናትና ምርምር የፈጠራ ስራዎች የማቅረብና የስፖርታዊ ውድድር ዛሬ ተጀምሯል።


የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንዳሉት ተማሪዎች ከቀለም ትምህርት ባሻገር የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባል።

ለዚህም ተማሪዎችን ከታች ጀምሮ በዝንባሌያቸው መሰረት እገዛ በማድረግ በጥናትና ምርምር እውቀትና ክህሎታቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የተማሪዎች የፈጠራ ስራ ቴክኖሎጂን ከሌሎች በመቅዳት ከማላመድ ባሻገር አዳዲስ ግኝቶች ላይ በማተኮር ለሀገራችን ብልጽግና የቀጣይ መሰረት መሆን እንዳለባቸው አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩም የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ለማሳደግ በሚሰሩ ስራዎች የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ነው ያሉት።


የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ ብዙነህ በበኩላቸው ውድድሩ ተማሪዎችን በምርምርና በስልጠና በማገዝ ብቁና ተወዳዳሪ ትውልድ ለመቅረጽ ያለመ ውድድር ነው ብለዋል።

በውድድሩ የግብርና ስራን የሚደግፉ የድሮን ቴክኖሎጂ የቱሪዝም ሀብትን የሚያስተዋውቁ እና ኢንቨስትመንትን የሚደግፉ 40 የፈጠራ ስራዎች በተማሪዎቹ መቅረባቸውን ገልፀዋል።


የሃይለማሪያም ማሞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሳሙኤል ዓለማየሁ እንዳለው በተለይ የአየር ብክለትን የሚከላከል ቴክኖሎጂ ለውድድር ይዞ ቀርቧል።

ተማሪ እንደሻው ይታገሱ በበኩሉ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ ዩኒቨርስቲዎችና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሊደግፉ እንደሚገባም ጠይቋል።

ይኸው የጥናትና ምርምር የፈጠራ ስራ እና ስፖርታዊ ውድድር ከመጋቢት 5 እስከ 7/2017 ዓም እንደሚቆይም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025