ባህርዳር፤ መጋቢት 7/2017(ኢዜአ)፡- በሀገራችን ምርታማነትን በማሳደግ አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ የፈጠራ ስራዎችን ለማዳበር በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ።
የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ የስልጠናና የስታርታፕ ውድድር መዝጊያ መርሃ ግብር በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ(ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በሀገሪቱ ምርታማነትን የሚያሳደጉና አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ የፈጠራ ስራዎችን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በሁሉም ዘርፍ የመንግስትንና የህዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቴክኖሎጂ በመፍጠር ጠንካራ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሚናው የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሚኒስቴሩ በወጣቶች የሚከናወኑ የፈጠራ ስራዎች(ስታርታፕ) አቅም እንዲጎለብት ተከታታይ ውድድሮችንና ስልጠናዎችን በመስጠት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ይህን ተግባር ለማሳካትም ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በእለቱም የአማራ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲሱን ሎጎና ሌሎች የአሰራር ሂደቶችን የማስተዋወቅ ስራ እንደሰራም ተመልክቷል።
በመድረኩም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴሩ ኃላፊዎችና የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025