አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ)፦ በህዝብ እና በጭነት አገልግሎት የተሰማሩ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን ብቃት መለካት የሚያስችል ሰነድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ገለጹ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን የብቃት ምዘናውን ካበለፀገው ኤስዲኤስ ከተሰኘው ተቋም አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባበር የአሽከርካሪዎችን ብቃት ለመመዘን ዝግጅት እያደረገ ነው።
ሚኒስትር ዴኤታው የትራፊክ አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር በሰው እና በንብረት ላይ የሚደርሰውን ውድመት ለመከላከል ለሚደረገው ርብርብ ከሰነዶች ዝግጅት ባሻገር ወደ ተግባር ሲገባ አሰራሩን ተፈፃሚ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቀጣይ ውይይቶች እንደሚደረጉም ገልጸዋል።
የብቃት ምዘናው በየደረጃው ተከፋፍሎ ይሰጣል።
በመጀመሪያ ዙር የአገር አቋራጭ አውቶቡሶችንና የድንበር ተሻገሪ የጭነት ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎችን ብቃት መለካት የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025