የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የበጋ መስኖ ስንዴ እና ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎች ለውጥ እያመጡ  ነው - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

Mar 19, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በበጋ መስኖ ስንዴና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎች እየመጡ ያሉ ውጤቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በቀነችና ኦፊያ አነስተኛ መስኖ በክላስተር 1 እና 2 በ86 ሄክታር መሬት የለማ የበጋ መስኖ ስንዴና በ192 ሄክታር መሬት የለማ የሽንኩርትና ሌሎች የፍራፍሬ ምርቶችን ተመልክተዋል።


ርዕሰ መስተደድሩ በጉብኝቱ ላይ እንዳሉት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ሰፊ ለውጦች ታይተዋል።

ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም መሬትና የውሃ አማራጮች በማልማት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በቤተሰብ ደረጃ እና የሀገር ውስጥ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ።

ወደ ውጭ የሚላኩ የግብርና ምርቶችን በስፋት በማምረት የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ እና በሀገር ውስጥ ለአግሮ ኢንዱስትሪ የሚቀርቡ ምርቶችን በስፋት ማምረት ትኩረት የተሰጠባቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

በጨና ወረዳ ሁለት አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ በመግባታቸው አርሶ አደሮቹ በ86 ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴ፣ የተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶችና አትክልቶችን ማልማታቸው የሚበረታታ መሆኑን በመስክ ምልከታ ወቅት ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ በሌሎች አከባቢዎችም 7 ዘመናዊ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታዎች ተገንብተው ወደ ሥራ ገብተዋል ያሉት ርዕሰ-መስተዳድሩ በበጋ መስኖ ስንዴና በሌሎች ምርቶች እየመጡ ያሉ ለውጦች እንደሚጠናከሩም ጠቁመዋል።

በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በ2ኛ ዙር መስኖና በበልግ 103 ሺህ ሄክታር ማሳ በማልማት ወደ 27 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የገለጹት ደግሞ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሠተዳድርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ናቸው።


5 ሺህ 50 ሄክታር ማሳ በበጋ መስኖ ስንዴ መልማቱን ጠቁመው ምርታማነቱንም በሄክታር ከ38 ኩንታል በላይ ለማድረስ መታቀዱንም መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025