
ቦንጋ፤ መጋቢት 9/2017 (ኢዜአ):-በአካባቢያቸው የተገነቡ የመስኖ አውታሮችን ተጠቅመው ካለሙት ስንዴ የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጨና ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶር)ና ሌሎች ከፍተኛ አመራር አባላት በጨና ወረዳ የለማ የበጋ መስኖ ስንዴና የአትክልት ልማትን ጎብኝቷል።
በዚህ ወቅት በወረዳው የቦባ ጎታ ቀበሌ አርሶአደር ገረመዉ ሀይሌ በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸው ዘመናዊ የመስኖ አውታር ባለመኖሩ በጋውን ለምርት እንደማይጠቀሙ አስታውሰዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአካባቢያቸው የተገነቡ ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን ተጠቅመው ለመጀመሪያ ጊዜ የበጋ መስኖ ስንዴ ያለሙ መሆኑን ገልጸው፤ አሁን ላይ የምርቱ ቁመናው ጥሩ እንደሆነና የተሻለ ምርት እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።
ሌላኛው አርሶ አደር ወጣት ፍቅሬ በቀለ በበኩሉ፤ ግማሽ ሄክታር ማሳ ላይ ስንዴ ማልማቱን ገልጿል።

በበጋው ወቅት ብዙም ውጤት በማይሰጡ የእርሻ ስራዎች ያሳልፉ እንደነበር አስታውሶ፤ የመስኖ አውታር ግንባታ ሳቢያ ዉሃ እንደልብ በማግኘት ልማቱን እያከናወኑ እንደሚገኝ ተናግሯል።
አርኦ አደሮቹ እንዳሉት፤ በኩታ ገጠም ማልማታቸው በጋራ የአረም ቁጥጥር ለማድረግ፣ ምርትን በጋራ ለመሰብሰብ እና ተደጋግፎ ለመስራት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በክልሉ የተገነቡ የመሰኖ ልማት አውታሮች የእርሻ ስራ ውጤታማነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።

በተለይም የክልሉ የእርሻ ስራን ስኬታማነት ለማረጋገጥ የውሃ አማራጭን ለመጠቀም መስኖ አውታሮች የማስፋት ስራ ውጤት እያመጣ መሆኑንና ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል ።
አርሶ አደሩ ከዝናብ ጠባቂነት በመላቀቅ የመሬትና የውሃ ሀብቶች በተገቢው ተጠቅሞ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጎልበት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው፤ በክልሉ መስኖን በመጠቀም ስንዴ፣ ሩዝና አትክልትን ጨምሮ ሌሎችንም የማልማቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

በክልሉ ዘንድሮ በሁለተኛ ዙር መስኖና በበልግ 103 ሺህ ሄክታር ማሳ እየለማ መሆኑን ጠቁመዋል።
ክልሉ ያለውን ፀጋ ወደ ልማት ለመቀየር እየተሰራ ነው ያሉት ደግሞ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን ናቸው።

አበረታች የልማት ስራዎች የማስፋትና የመደገፍ ስራ ይጠናከራል ነው ያሉት ።
በክልሉ ውስጥ ያሉ ፀጋዎችን ወደ ሀብትነት ለመቀየርና ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ ወጥነት ባለው መልኩ የመደገፍ ስራ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
በጉብኝቱ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራር አባላት፣ ሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
ሀዋሳ፤ ሰኔ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀዋሳ ከተማን በማልማት የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ማዕከልነቷን ይበልጥ ለማሳደግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Jun 14, 2026
ጋምቤላ፤ ሰኔ 3/2018(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የመኸር እርሻ ለማልማት ከታቀደው ውስጥ ከ72 በመቶ በላይ የሚሆነው መሬት በዘር መሸፈኑን የክልሉ ...
Jun 11, 2026
ደብረ ማርቆስ ፤ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሰብል ልማት ጎን ለጎን በተከናወነ የንብ ማነብ ስራ ወደ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚጠጋ የማ...
Jun 4, 2026
ዲላ፤ ግንቦት 16/2018 (ኢዜአ)፡-ከ40 በላይ የንግድ ተቋማትና አጋር አካላት ተሳትፈውበት በዲላ ከተማ የተዘጋጀው "ቡኖ - ማላ" ኤክስፖ ምርቶችን እና የኢ...
May 25, 2026