የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኮደርስ ስልጠናው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎትን ያሳደገ ነው

Mar 20, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ)፦ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎታቸውን በማላቅ በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚረዳቸው መሆኑን ስልጠናውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ወጣቶች ገለጹ።

ስልጠናው ለሚሰሩት ስራ ተጨማሪ አቅምን እንደሚፈጠረላቸውም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም የአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ኤኒሼቲቭ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

ኤኒሼቲቩ "ትውልድ ይማር፣ ትውልድ ይሰልጥን፣ ከዓለም ጋር ይፎካከር" በሚል እሳቤ ወጣቶች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማዳበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ለማድረግ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

ኤኒሼቲቩ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው።

ስልጠናውን ያጠናቀቁ ወጣቶች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ከሚፈጠሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋር ራሳቸውን በፍጥነት እንዲያራምዱ የኮደርስ ስልጠናው ወሳኝ ነው፡፡

ከስራዋ ጎን ለጎን አራቱንም ስልጠናዎች በማጠናቀቅ ምስክር ወረቀት ያገኘችው ትዕግስት ጉዱ እንዳለችው ስልጠናው ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ ነው።

ስልጠናው ከፅሁፍ በተጨማሪ በምስል ተደግፎ መሰጠቱ ሳቢ እንደሚያደርገው የገለፀው ይድነቃቸው ተስፋዬ በበኩሉ በስልጠናው ያገኘው እውቀት ለሚሰራው ስራ ተጨማሪ አቅም መሆኑን ተናግሯል።

ስልጠናው በአለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብት በመሆኑ እድሉን በመጠቀም ራስን ከዘመኑ ጋር ማዘመን ያስፈልጋል ብለዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው በመዲናዋ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት በአምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ መርሃግብር 300ሺህ ነዋሪዎችን ለማብቃት ታቅዷል ብለዋል።

ስልጠናው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ ከ165 ሺህ በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን እየተከታተሉ ሲሆን 56 ሺህ ያህሉ ደግሞ ምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

ስልጠናው የዲጂታል ክህሎትን በማበልጸግ ስማርት ሲቲን ለመፍጠር የሚያግዝ በመሆኑ በከተማዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ቢሮዎች ሰራተኞቻቸው ስልጠናውን እንዲከታተሉ ማበረታታት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025