
ባህርዳር ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል ለመጪው መኸር ጥራቱ የተጠበቀ ዘር ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ትኩረት መደረጉን የክልሉ የግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን አስገነዘበ ።
አርሶ አደሩ የዘር ጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበትን ትክክለኛ ዘር ለይቶ ሊጠቀም እንደሚገባም ባለስልጣኑ አሳስቧል።
በባለስልጣኑ የዘር ጥራትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ጉርሜሳ እጀታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በክልሉ በባለፈው የምርት ዘመን በ12ሺህ 791 ሄክታር መሬት ላይ 18 አይነት የሰብል ዘር የማባዛት ስራ ተከናውኗል።
የዘር ብዜት ስራውም በመንግስት፣ በድርጅቶች፣ በዩኒየኖች፣ በምርምር ማዕከላት፣ በዩኒቨርስቲዎችና በግልለሰቦች ደረጃ መከናወኑን ገልጸዋል።
በማባዣዎች ከተመረተው ዘር ውስጥ 220ሺህ 371 ኩንታል ዘር ጥራቱን ጠብቆ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ።
ከተሰበሰበው ውስጥም 190 ሺህ ኩንታል ዘር ተበጥሮ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
የተበጠረውን ዘር በላብራቶሪ በማረጋገጥ የጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበት መሆኑን ጠቁመው የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍና ሌሎች የሰብል አይነቶች ይገኙበታል ብለዋል።
አርሶ አደሩም በመጪው የመኽር ወቅት የዘር ጥራት ማረጋገጫ የተለጠፈበትን ትክክለኛ ዘር በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን እንዲያሳድግ መልእክት አስተላልፈዋል።
ባለፈው ምርት ወቅት በበቆሎ ዘር ብቻ ተለጥፎ ይቀርብ የነበረው የጥራት ማረጋገጫ ዘንድሮ በሁሉም የሰብል አይነቶች በመለጠፍ የሚቀርብ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026