አዲስ አበባ፤መጋቢት 11/2017 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎች ጋር ባደረገችው የ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የእዳ ሽግሽግ ማግኘቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፥ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ማሻሻያውን ተከትሎ ጤናማ የእዳ አስተዳደር እንዲኖር እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
በዚህም ከአበዳሪዎች ጋር በተደረጉ ድርድሮች ኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የእዳ ሽግሽግ ማግኘቷን አመልክተዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ባለባት የእዳ ጫና ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ አግባብነት የሌላቸው እዳዎች እንዲሰረዙ እና በአፍሪካ ላይ የተጫነው እዳ እንዲቃለል መስራቷን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025