አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2017(ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስከ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና መስጠት የሚያስችል አቅም አለ ሲሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ ገልጸዋል።
በክልሉ በ5ሚሊዮን ኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዲጂታል ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ መፍጠር በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ያስችላል ብለዋል።
በኢኮኖሚና በስልጣኔ ተወዳዳሪ ለመሆን ብቃት ያለው እና የሰለጠነ ዜጋ መፍጠር ተገቢ መሆንም ገልጸዋል።
በክልሉ በዘርፉ የወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማሳደግ ስልጠናው ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።
በክልሉ እስከ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች ስልጠና መስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለ ገልጸው
ወጣቶች በነጻ የተገኘውን እድል መጠቀም እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ዜጎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባቦት መፍጠር እንዲችሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ኃላፊው ለዚህም የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት የተገኘው የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት እና የእድገት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውም አብራርተዋል።
መንግስት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን ስልጠና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያመቻቸውን ነጻ እድል መጠቀም እንደሚገባም አቶ አንተነህ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ በየደረጃው ያለው አመራር እና ባለሙያ በስልጠናው መሳተፍ እንዳለበት ጠቁመው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችም በነጻ የተገኘውን እድል መጠቀም እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው እንደ ክልል በኢትዮ ኮደርስ የስልጠና እድል ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በክልሉ ስልጠናውን በሚፈለገው መጠን እና ጊዜ መስጠት እንዲቻል ከርዕሰ መስተዳድሩ ጀምሮ አጠቃላይ አመራሩ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዲጂታል ቴክኖሎጂው ጋር የተላመደ ማህበረሰብ ለመፍጠር የስልጠናው አስፈላጊነት የጎላ መሆኑን መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ህብረተሰቡ በጊዜና በቦታ ሳይገደብ ስልጠናውን መከታተል የሚችልበት ስርዓት መዘርጋቱን የተናገሩት ኃላፊው ኢትዮ ቴሌኮም ስልጠናው ስኬታማ እንዲሆን ነጻ የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረቡ አመስግነዋል።
የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ በበኩላቸው በክልሉ ለዜጎች የሚሰጠው ስልጠና ውጤታማ እንዲሆን የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረት ይጠይቃል ነው ያሉት።
በአፈጻጸም በኩል የተስተዋሉ መልካም ልምዶችን ማስቀጠል እና ውስንነቶችን በማረም ስልጠናው የዜጎችን ህይወት መቀየር እንዲችል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025