አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- የለውጡ ትሩፋት የሆነው የጥራት መንደር በዓመት ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የገቢና ወጪ ንግድ ምርቶችን ጥራት የማረጋገጥ አስተማማኝ አቅም መፍጠሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ባለፉት ሰባት ዓመታት የንግድና የምርት ጥራት ፍተሻ መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላትን የጥራት መንደር ባለፈው ህዳር ወር 2017 ዓ.ም መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ የጥራት መንደር ለዘላቂ ዕድገት መሰረት የሚጥልና የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጅማሮ የሚያበስር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የጥራት መንደር የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣንን የያዘ ነው፡፡
ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር)፥ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የጥራት ቁጥጥር የማድረግ አቅም በእጅጉ ተሻሽሏል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ዘርፉን ዕድገትና ተወዳዳሪነት ለማሻሻል፥ በአፍሪካ ግዙፉን የጥራት መንደር መገንባቷን አንስተዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ሰጪነትና በጋራ ጥረት እውን የሆነው የጥራት መንደር ዓለም ከደረሰበት ደረጃ ጋር የሚሄዱ ዘመናዊ የፍተሻ ላቦራቶሪዎች የተገጠሙለት መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት ኢትዮጵያን በወጪ ንግድ በአፍሪካ ቀዳሚ ለማድረግ የያዘውን ራዕይ ለማሳካትም፥ የለውጡ ትሩፋት የሆነው የጥራት መንደር ወሳኝ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ጥራት ማረጋገጫና የፍተሻ መሰረተ ልማት፥ የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን የማድረግ ጉዞን ለማሳካት የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የጥራት መንደር በዓመት ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ቶን በላይ ገቢ እና ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን የወጪ ንግድ ምርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ፍተሻ የማድረግ አስተማማኝ አቅም መፍጠሩንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ካሏት የጥራት ደረጃዎች 80 በመቶ ያህሉ ከዓለም አቀፉ ደረጃዎች ጋር የተጣጣሙ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ይህም ሀገሪቱ በዓለም የንግድ መስተጋብር የተሻለ ተሳትፎ እንዲኖራት ያስችላል ብለዋል፡፡
የጥራት መንደር ኢትዮጵያ በጥራት ፍተሻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጎልታ የምትታይበትን እድል የፈጠረ መሆኑንም ገለጸዋል፡፡
ዘመናዊ የፍተሻ መሣሪያዎችን በማሟላት የተሻሻለ አቅም የፈጠረው የጥራት መንደር ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር ተስማሚ ጥራት እንድታረጋግጥ፣ የቴክኒክ መሰናክሎችን እንድትቀንስና በዓለም አቀፍ ንግድ ያላትን ተሳትፎ እንድታሻሽል ጉልህ አስተዋፅኦ አለው።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025