አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፦ የለውጡ መንግሥት ለመስኖ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በሟቋቋም የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ ሰርቷል ሲሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ገለጹ።
እንደ ሀገር ውጤታማ የሆነ የፕሮጀክት አፈጻጸም የለውጡ መንግሥት መለያ ባህሪ ነው ሲሉም አክለዋል።
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች መጋቢት 24ን በፓናል ውይይት እክብረዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ(ዶ/ር) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የተወለደው ለውጥ ትላንትን ያልረሳ፣ የዛሬን ያከበረ፣ ለነገ እርሾ ያስቀመጠ ነው በለዋል።
ለውጡ ቀደም ብለው የነበሩ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በተሟላ ዴሞክራሲያዊ ምህዳር የፈታ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላከትል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም እንደ ሀገር ውጤታማ የሆነ የፕሮጀክት አፈጻጸም የለውጡ መንግሥት መለያ ባህሪ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የለውጡ መንግሥት ለመስኖ ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በሟቋቋም የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ ሰርቷል ሲሉም ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የተጠናቀቁ፣ በመጠናቀቅ ላይ ያሉና በሂደት የሚጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም አብራርተዋል፡፡
ከለውጡ ማግሥት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸው የፍትህና ጸጥታ ተቋማትን ያሻሻለ፣ የኢኮኖሚ ስብራትን የጠገነ፣ ሁሉም ዜጎች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ሁነቶች ላይ ያሳተፈ፣ ለትውልድ የሚተርፍ ምንዳ በማስቀመጥ ለውጥ ማምጣት ችለናል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ እንድርያስ ጌታ(ዶ/ር) ለውጡ ፈተናዎችን ተሻግረን ስኬቶች ያስመዘገብንበት፤ ያጋጠሙ ችግሮችን በድል የተሻገርንበት፤ ነጻና ገለልተኛ ምርጫ ተካሂዶ ሁሉንም ያካተተ መንግሥት የተመሰረተበት፤ ሀገራችን አደጋ ላይ በወደቀች ጊዜ ሕዝብን በማስተባበር ፈተናን የተሻገርንበት በመሆኑ በድምቀት እያከበርነው እንገኛለን ነው ያሉት፡፡
ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በበኩላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ለውጥን ለማጽናት ተልዕኮ የተሰጠን በመሆናችን የተቋማችንን ተልዕኮ ዕውን ለማድረግ በጋራ መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አብዱረህማን አብደላም እንዲሁ ባለፉት ሰባት ዓመታት የታየው ለውጥ የኢትዮጵያን ዕጣ ፋንታ ብሩህ ያደረገ፤ ዘርፈ ብዙ ስብራቶችን የጠገነ፤ የልማትን ቀጣይነት ያረጋገጠ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮችና ሠታተኞች ለኢትዮጵያ ብልፅግና ስኬት በግንባር ቀደምትነት የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ቃል መግባታቸውንና የደም ልገሳ መርሃ ግብር መከናወኑን በመረጃው ተጠቁሟል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025