
ሚዛን አማን ፤መጋቢት 24/2017 (ኢዜአ):-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ የግብርና ቢሮ አስታወቀ።
ዛሬ በሚዛን አማን ከተማ በዶሮ መንደር ለተደራጁ ሴቶች ዘመናዊ የዶሮ ቤት የማስረከብ ሥነ ሥርዓት ተካሄዷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና አማካሪ አቶ ዮሐንስ መላኩ እንዳሉት በከተሞች የሚታየውን የእንቁላል ምርት እጥረት ለመቅረፍ በዶሮ እርባታ የተደራጁ መንደሮችን ሞዴል ለማድረግ እየተሠራ ነው።
በዘንድሮ በጀት ዓመት ከ5 ነጥብ 6 ሚሊዮን በሚበልጥ በጀት 600 ዘመናዊ የዶሮ ቤቶችን በሚዛን፣ በቴፒ፣ በቦንጋና በታርጫ ከተሞች በዶሮ መንደር ለተደራጁ ግለሰቦች ይሠራጫል ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ በሚዛን አማን ከተማ 30 ሆነው ለተደራጁ ሞዴል የዶሮ አርቢዎች ሥልጠና በመስጠት ዘመናዊ የዶሮ ቤት ማስረከባቸውን ገልጸዋል።
በሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እና የእንስሳት ሀብት ውጤታማነት ምጣኔን ከፍ የማድረግ ግብን ለማሳካት በሌሎችም ዘርፎች መሰል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስገንዝበዋል።
በክልሉ ከ500 በላይ የዶሮ መንደሮች በከተማና በገጠር መኖራቸውን አቶ ዮሐንስ ጠቅሰዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም በበኩላቸው በሌማት ትሩፋት ሥራ እየተገኘ ያለውን እንቁላል ኅብረተሰቡ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል የመሸጫ ቦታ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ክልሉ ዛሬ ያደረገው ድጋፍ ተግባሩን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ነው ያሉት ከንቲባው እንደ ከተማ አስተዳደሩ የዶሮ መንደሩን ውጤታማ ለማድረግ ክትትልና ድጋፍ እናደርገለን ብለዋል።
የዶሮ ቤት ድጋፍ ከተደረጋላቸው ሴቶች መካከል ወይዘሮ ፍጹም ሰዒድ በተረከቡት የዶሮ ቤት 50 ዶሮዎችን ለማርባት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
አሁን ላይ ካላቸው 10 ዶሮዎች የሚያገኙትን እንቁላል ለቤት ቀለብ እንደሚጠቀሙ ገልጸው በቀጣይም አስፋፍተው ወደ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ለመሆን ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
የተሰጣቸው ዘመናዊ የዶሮ ቤት ዶሮዎች በአውሬ እንዳይበሉ ከማድረግ ባሻገር የራሱ የሆነ መመገቢያና እንቁላል መጣያ ያለው በመሆኑ ምቹ ነው ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ትዝታ ወዛብ ናቸው።
መንግሥት እያደረገ ባለው ድጋፍ ተበረታተው ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመለወጥ የሚያስችል ሥራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ከዶሮ ቤት ማስረከብ ሥነ ሥርዓት በኋላ በሚዛን አማን ከተማ እንቁላል በማምረት ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ምልከታ ተደርጓል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026