የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በለውጡ አመታት የተገኙ ስኬቶችን ለማስፋት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ማጠናከር ይገባል

Apr 7, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 26/2017(ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሰባት አመታት በለውጡ አመታት የተገኙ ስኬቶችን ለማስፋት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ።

የሰባት አመታት የለውጥ ጉዞና የተገኙ ውጤቶችን የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ በኦሮሞ ባህል ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአውደ ርዕዩን የጎበኙ አካላት በለውጡ ዓመታት በበርካታ ዘፎች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፥ እነዚህ ውጤቶች የበለጠ እንዲጠናከሩ በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ይገባል ብለዋል።

አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል አቶ አብዲሳ ታደሰ፥ በለውጡ አመታት በክልሉ በተለያዩ ተቋማት የቀረቡ የልማት ውጤቶች ወደ እድገትና ከፍታ እየተራመድን መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

እነዚህን የልማት ውጤቶች በቴክኖሎጂ በመደገፍ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ጠቅሰው በዚህ ረገድ ሁሉም የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

አቶ ዮናታን ጫሊ በበኩላቸው፥ በለውጡ አመታት በሁሉም መስኮች የተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተው፥የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህ የልማት ውጤቶች የተገኙት በብዙ ውጣ ውረድ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከዚህ ልምድ በመውሰድ ስራዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉ እንዲሆኑ መትጋት ይገባልም ብለዋል።

ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ደረጀ ጥላዬ በበኩላቸው፥ በክልሉ በተለይም በግብርና፤ በትምህርትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተስፋ ሰጪ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በግንባታ ዘርፍ ላይ በቴክኖሎጂ የመጡት ለውጦች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው ይበልጥ ለማስቀጠል በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮችን መዘርጋትና ማስፋት ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ባለፉት ሰባት አመታት የኦሮሞን ባህልና ትውፊት የሚገልጹ የተለያዩ ቅርሶች ካሉበት ተሰብስበው ለቱሪዝም አገልግሎት እንዲውሉ መደረጉን የተናገሩት ደግሞ በኦሮሞ ባህል ማዕከል የሙዚየም ልማትና የተንቀሳቃሽ ቅርስ ቡድን መሪ ወይዘሮ ቅድስት ለገሰ ናቸው።

ለወደፊቱም ያሉንን ሀብቶች በቴክኖሎጂ በማዳበርና በማስተዋወቅ ገቢ እንዲያመጣ እንሰራለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025