የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል የድርሻችንን እየተወጣን እንገኛለን - ዋና ኦዲተሮች

Apr 7, 2025

IDOPRESS

ድሬዳዋ፤ መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን የክልሎችና የከተሞች ዋና ኦዲተሮች ገለፁ።

በድሬዳዋ የተካሄደው 10ኛው የክልሎች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የምክክርና የልምድ ልውውጥ መድረክ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ተጠናቋል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው ዋና ኦዲተሮች የመንግስትና የህዝብ ሃብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ሀላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በድሬዳዋ ለሁለት ቀናት የተደረገው የልምድ ልውውጥና ምክክርም የኦዲት ስራ ጥራትን ለማረጋገጥ አቅም የፈጠሩበት እንደሆነም ተናግረዋል።


ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የሐረሪ ክልል ዋና ኦዲተር አቶ አብዱማሊክ በከር እንዳሉት፤ በክልሉ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ጥብቅ የኦዲት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ ቢሻው በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ወጥ የሆነ የኦዲት ስራን ለመተግበር መደላድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

ከምክክር መድረኩ በኦዲት ስራዎች ላይ የገጠሙ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ልምዶች በመቅሰማቸው በቀጣይ የተሻለ የኦዲት ስራዎችን ለማከናወን የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚያግዛቸው ጠቁመዋል።


ከድሬዳዋ የቀሰሙትን ልምድ በመቀመርና በመተግበር ፈጣንና ቀልጣፋ የኦዲት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አቅም እንደሚሆናቸው የገለፁት ደግሞ የሲዳማ ክልል ዋና ኦዲተር አቶ ሲምቦ ሽንብሩ ናቸው።

ባገኙት ተሞክሮም በቀጣይ የህዝብና የመንግስት በጀት በትክክል ስራ ላይ እንዲውል ጥራት ያለውና አመኔታ ያተረፈ የኦዲት አገልግሎትን ለውሳኔ ሰጪ አካላት ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።


የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ኦዲተር አቶ ንጉሱ ገብረ ጊዮርጊስ በበኩላቸው በክልሉ በትላልቅ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተገቢውን የኦዲት ስራ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩ የኦዲት አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላችውም ገልጸዋል።


የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ዋና ኦዲተሮችና ዳይሬክተሮች ከምክክር በኃላ በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ መሠረተ ልማቶችንና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025