
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 27/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬትና መዋቅራዊ ሽግግር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
በሹዋሊድ ክብረ በዓል ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመሆን በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም በክልሉ ያለው የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ፤ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የድንገተኛ አደጋ ማዕከልና የሲሲ ቲቪ የመንገድ ላይ የደህንነት ካሜራ ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ማስ ኢንጅነሪንግ ድርጅትን በጎበኙበት ወቅት እንደገለፁት በክልሉ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬትና መዋቅራዊ ሽግግር የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል እየተሰራ ነው።
በተለይም ከለውጡ ወዲህ የአምራች ዘርፉን ችግሮች በመለየት በተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች የተሻለ መነቃቃት መፈጠሩን ገልፀዋል።

ይህም ከለውጡ በፊት በነበረው የፖለቲካ መጠፋፋት የተፈናቃዮች መጠለያ የነበሩ ሼዶች አሁን ላይ የምርት ማዕከል በመሆን የአገርን ልማት ሊደግፉ የሚችሉ ስራዎች እየተሰራባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት በኢንዱስትሪ ዞኑ የሚመረቱ የመንገድ ዳር መብራቶች የሐረር ከተማ ኮሪደሮችን ከማድመቅ ባሻገር ለጥገና ምቹ እና ተመራጭ መሆናቸወንም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በከተማው ገቢራዊ እየሆኑ የሚገኙ የመንገድ ላይ የደህንነት ካሜራዎችና የድንገተኛ አደጋ ማዕከል ከከተማው ዕድገት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎች እና ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል ያስችላሉ ብለዋል።
በተለይ ከእሳት አደጋ ጋር ተያይዞ ከማህበረሰቡ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገልፀዋል።
በጉብኝቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልል ቅርንጫፍ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፤ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፤ የሐረሪ ጉባኤ አፈ-ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፤የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን የክልል ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026