ባህርዳር፤መጋቢት 28/2017 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ በግብአትነት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ የማድረስ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ሕብረት ስራ ማሕበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ የግብዓትና ግብይት ዳይሬክተር አቶ አለምዘውድ ስሜነህ፤ ክልሉ ለማስገባት ያቀደውን ስምንት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ፈጥኖ ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት አሰራር ዘርግቷል።
እስካሁን ወደ ክልሉ ከገባውን ሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ውስጥ አንድ ነጥብ ሰባት ኩንታል የሚሆነውን በሕብረት ስራ ማሕበራት አማካኝነት ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን አስታውቀዋል።
በቀጣይም የሚገባውን ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ በማሰራጨት የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በባህርዳር የሚገኘው የመርከብ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው እሸቱ በበኩላቸው፥ ዩኒየኑ ለምርት ዘመኑ አንድ ሚሊዮን 335 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለማሰራጨት አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከቀረበው 350 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 80 ሺህ ኩንታሉን በሰሜን ጎጃም ዞን፣ በባህርዳር ከተማ አስተዳደርና በከፊል ደቡብ ጎንደር ዞን አርሶ አደሮች መሰራጨቱን አስረድተዋል።
ለመጪው የመኽር ወቅት 703 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለማሰራጨት ግብ ይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በሰሜን ሸዋ ዞን የወደራ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ አስገልለው ሙሉሸዋ ናቸው።
ዘንድሮ ወደ ዩኒየኑ መጋዘን የቀረበውንና የከረመውን ጨምሮ 222 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት መቻሉን ጠቁመው፥ የስርጭቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል።
በሰሜን ጎጃም ዞን የአዴት ወረዳ አርሶ አደር ይሁን እለሙ በሰጡት አስተያየት፥ ለመጪው መኸር ቀድሞ ለሚዘራው የበቆሎ ሰብል አንድ ኩንታል ማዳበሪያ መግዛታቸውን ጠቁመው፥ ማዳበሪያው ቀድሞ መድረሱ ተረጋግተው እንዲሰሩ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።
አሁን ላይ ያለአፈር ማዳበሪያ የሰብል ምርታማነትን ማሳደግ አይታሰብም ያሉት ደግሞ በዚሁ ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ አርሶ አደር አቶ ልየው አድማሱ ናቸው።
በምርት ዘመኑ በተለያየ ሰብል ለሚያለሙት ሁለት ሄክታር ተኩል መሬታቸው ሶስት ኩንታል ተኩል የአፈር ማዳበሪያ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሰዋል።
የማዳበሪያ ግብአቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ቀበሌያቸው መቅረብ በመጀመሩ ቀድመው በመግዛት የሰብል ልማታቸውን ለማካሄድ መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል።
በክልሉ በ2017/2018 የመኸር ምርት አምስት ነጥብ አራት ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ187 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል።
ከህብረት ስራ ማበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ በአማራ ክልል በ2016/2017 የምርት ዘመን ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025