የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ በመኽር ወቅት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም ይለማል

Apr 7, 2025

IDOPRESS

ደሴ፤መጋቢት 28/2017(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመኽር ወቅት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም በማልማት የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።


ቢሮው የ2017/2018 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ልማት እቅድን ለማሳካት በግብርና ፓኬጅ አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠናና የእቅድ ትውውቅ ማጠቃለያ መድረክ በደሴ ከተማ አካሂዷል።


የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፥ በክልሉ የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው።


በዚህም በመኽር ወቅቱ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በኩታገጠም በማልማት 115 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።


ይህም በምርት ወቅቱ አጠቃላይ 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር በመሸፈን ከ187 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ የተያዘውን ግብ ለማሳካት አጋዥ እንደሚሆን አስረድተዋል።


ከኩታ ገጠም አስተራረስ ባሻገር አሲዳማ መሬት በኖራ በማከም፣ግብዓት በማቅረብ፣መካናይዜሽንን በማስፋፋትና ሌሎችም ተግባራት በማከናወን የታቀደውን ምርት ለማግኘት ከወዲሁ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።


ይህም በምግብ ራስን ለመቻል፣ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃና ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶችን በብዛትና በጥራት በማምረት ግብርናው የሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች መሰረት መሆኑን ለማረጋገጥ አላማ ያደረገ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።


በመድረኩ የክልል፣የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራር አካላት፣ የግብርና ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው</p>

አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...

Feb 28, 2025

<p>በተሰማራንበት መስክ ውጤታማ በመሆናችን ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ማደግ ችለናል</p>

ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...

Feb 28, 2025

<p>ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው-ቋሚ ኮሚቴዎቹ</p>

አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...

Feb 12, 2025

<p>የማዕከሉ መገንባት በክልሉ የሚስተዋለውን የምርጥ ዘር ችግር በዘላቂነት ይቀርፋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...

Feb 8, 2025