
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ የቻይና ባለሀብቶች በጅማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ ከመንግስት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ገለጹ።
አምባሳደር ቼን ሃይ የጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን ጎብኝተዋል።
አምባሳደሩ በጅማና አካባቢው በስፋት የሚመረተውን አቮካዶ በግብዓትነት በመጠቀም ወደ አውሮፓና አሜሪካ ገበያዎች የሚልከውን አክሻይ ጀይ ኩባንያ የምርት ሂደትና አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በጅማና አካባቢው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ማቀነባበር የሚያስችል መብራት፤ ውሃ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መኖራቸውን ከጉብኝቱ መረዳት መቻላቸውን ተናግረዋል።
ቻይናውያን ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ከኮርፖሬሽኑ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ በበኩላቸው የቻይና ባለሃብቶች ተሳትፎ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ነጻ የንግድ ቀጣና ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እያደገ የመጣና ቀዳሚ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ጋር በኢንቨስትመንት እንዲሁም በሰው ሃብት ልማት፤ በእውቀትና ክህሎት ሽግግር ጭምር ያለውን ትብብር ለማጠናከር በቅርበት እየሰራ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት በመሸጋገር ሂደት ላይ ያሉ ተጨማሪ የኢንቨስትመንትና በመንግስት እየተወሰዱ ያሉ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሪፎርም ተግባራትን አንስተዋል።
ቻይናውያን ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ምቹ አማራጮችን ተጠቅመው በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026