
ነቀምቴ፤ መጋቢት 30/2017 (ኢዜአ):- በምስራቅ ወለጋ ዞን በየ2017/18 የምርት ዘመን የሚውል ከ230 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በምስራቅ ወለጋ ዞን ግብርና ፅህፈት ቤት የግብርና መካናይዜሽን የግብዓት ፍላጎት እና አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ለሚ አጋ እንዳሉት በየ2017/18 ምርት ዘመኑ 800 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ ነው።
በእስካሁኑ ሂደት 65 ሺህ 378 ኩንታል 'ዳፕ' እና 165 ሺህ ኩንታል 'ዩሪያ' የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል።
እንዲሁም 20 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ የታቅዶ ሲሆን እስካሁን 10 ሺህ 50 ኩንታል ለአርሶ አደሩ መድረሱን ጠቅሰው ያለውን ፍላጎት ለሟሟላት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የስርጭቱ ሂደት ከመልካም አስተዳደር ችግር በጸዳ መልኩ እንዲከናወን ሽያጩ በዲጂታል መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አስፋው ሀንቢሳ፤ በዞኑ በተለያዩ ኢኒሼቲቮች አመቱን ሙሉ የግብርና ስራ እንዲከናወን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።
በዚህም የዞኑ አርሶ አደር በምግብ ራሱን ከመቻል ባሻገር ለሀገር ውስጥና እና ለውጪ ገበያ የሚውሉ ምርቶችን ማምረት መጀመሩን ጠቁመዋል።
በዞኑ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ እንዲቀርብ ከማድረግ ባሻገር አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጀት እንዲችል ያልተቋረጠ የባለሙያዎች እገዛ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው አንስተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026