ደሴ ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በዘንደሮ የበጋ ወቅት ከ50 ሺህ 600 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ በመስኖ የለማ የስንዴ ሰብል መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ለኢዜአ እንደገለጹት፤በክልሉ ያሉትን የውሃ አማራጮች በመጠቀም በዘንድሮው የበጋ ወቅት ከ202 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ለምቷል፡፡
እስከ አሁንም ከ50 ሺህ 600 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ ለምቶ የደረሰ ሰብል መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል።
አርሶ አደሩም የደረሰውን ቀሪ ሰብል እየጣለ ካለው ዝናብ ለመከላከል በፍጥነት መሰብሰብ እንዳለበት አሳስበዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ የ07 ቀበሌ አርሶ አደር ሰይድ አሊ በሰጡት አስተያየት፤ በአንድ ሄክታር ከሩብ ማሳቸው ላይ በመስኖ ያለሙትን ስንዴ መሰብሰባቸውን ገልጸዋል፡፡
በበጋ መስኖ አንድ ሄክታር የሚጠጋ መሬት ላይ ያለሙት ስንዴን እየሰበሰቡ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ በቃሉ ወረዳ 032 ቀበሌ አርሶ አደር ይማም አደም ናቸው፡፡
የደረሰውን ሰብል በጥንቃቄ በመሰብሰብ ከ20 ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠብቁም ጠቁመዋል፡፡
በአማራ ክልል ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ በስንዴ ሰብል ከለማው 159 ሺህ ሄክታር መሬት ከአምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በ2017/2018 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ልማት እቅድን ለማሳካት በግብርና ፓኬጅ አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠናና የእቅድ ትውውቅ ማጠቃለያ መድረክ ሰሞኑን በደሴ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025