አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ):- ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውንና እጅግ ፈጣን የሆነውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አገልግሎት ዛሬ በአዲስ አበባ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ለሀገር እድገት ቁልፍ የሆኑ ዘርፎችን የማዘመን ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
ከመገናኛ - ቦሌ አንበሳ ጋራጅ ፊት ስራ የጀመረው ጣቢያ የአውሮፓ ስሪት የሆኑ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙላት የሚያስችል እጅግ ፈጣን (EU Altra Fast) አቅም ያለው መሆኑም ተጠቁሟል።
የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎቹ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል በመሙላት በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል የመሙላት አቅም እንዳላቸው ተመላክቷል።
እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዛዝ በመተንተን የባትሪውን ደህንነት እየፈተሸ የተሽከርካሪው ባትሪ በሚችለው ፍጥነት ቻርጅ እንደሚያደርግም ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።
የኤሌክትሪክ ጣቢያው ለ24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥና አገልግሎቱን በቴሌብር ሱፐርአፕ አማካኝነት መጠቀምና የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል።
ኩባንያው ቀደም ሲል 16 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል ጣቢያ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውሶ ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ሺህ 280 የኤሌክትሪክ መኪኖች በኪሎ ዋት 376 ሺህ 575 ኃይል ቻርጅ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።
ይህም የአየር ብክለትን ከመከላከል አንጻር ከ521 ሺህ በላይ ኪሎ ግራም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ ማድረግ መቻሉንና ይህም ከ2 ሺህ 622 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር የሚስተካከል እንደሆነ አመልክቷል።
አዲሱ የመሙያ ጣቢያ 16 መሙያዎችን ማካቱንና ይህም ኩባንያው ያሉትን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም ወደ 32 ማድረስ መቻሉን አብራርቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለዘላቂ እድገት ወሳኝ የሆኑ ቀጣይነት ያላቸው የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን እና ፈጠራዎችን በማስተዋወቅ ለሀገር እድገት ቁልፍ የሆኑ ዘርፎችን የማዘመን ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025