አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1/2017(ኢዜአ)፦ የውሃ ቆጣሪ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት በማሟላት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የውኃ ቆጣሪ ምርት ላይ የተሰማራውን ሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግን ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት፤ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች በስፋት እንዲመረቱ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም በኢንጂነሪንግ ዘርፍ እና በሌሎች ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎችን የማስፋፋት እና የማጠናከር ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ የጎበኙት የውኃ ቆጣሪ ማምረቻ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማስቀረት በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም በሚቀጥሉት አመታት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን በማሟላት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የሚያመርቱ ፋብሪካዎች እንዲስፋፉ ከማድረግ አንጻር ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት ከተሞችም ጭምር የተለያዩ የፋብሪካ ምርቶች የሚመረትባቸው መሆን እዳለባቸው ተናግረዋል።
የሳቢያን ቤዝ ሜታል ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስራ አስኪያጅ ዐይንእሸት አስረስ(ዶ/ር) በበኩላቸው ድርጅቱ በቀን ከ800 እስከ 1000 የውሃ ቆጣሪ እያመረተ ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ ይገኛል ብለዋል።
በቀጣይም የምርቱን መጠን በማሳደግ ወደ ጎረቤት ሀገራት በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትየጵያ ታምርት ንቅናቄ ለውጤታማነታቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን አንስተው የመንግስት ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
አሶሳ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ):- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የትውልዱ አሻራና ኩራት ነው ሲሉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱልሙህሲን ሐሰን...
Feb 28, 2025
ሚዛን አማን፤የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በማህበር ተደራጅተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በመ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤የካቲት 4 /2017(ኢዜአ)፦ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ም...
Feb 12, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- የቦንጋ የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል መገንባት በክልሉ ለግብርና ስራው መሠረታዊ የሆነ...
Feb 8, 2025