
አሶሳ፤ሚያዝያ 1/2017(ኢዜአ):-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ።
ዘጠነኛው ክልል አቀፍ የግብርና ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የአርሶ አደሩን የግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አርሶአደሩ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ የግብዓት አጠቃቀም ባህሉን በመቀየር በምርት ዘመኑ አበረታች የግብርና እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ጠቅሰዋል።
ህብረተሰቡን ከተረጂነት ለመላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀረፁ የልማት ኢንሼቲቮችም ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን ጠቁመው፤በተለይም በሌማት ትሩፋት እና በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የተገኙ ውጤቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
ለአብነትም የፈሳሽ ናይትሮጂን ምርት መጀመርና የእንስሳት መኖ አቅርቦት ማሻሻልም የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸውን አብራርተዋል።
የክልሉ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ ካርታ የግብርናውን ዘርፍ ከዚህ በተሻለ እንደሚያሳድገውም አቶ አሻድሊ ጠቁመዋል።
አርሶ አደሩ የኩታ ገጠም እርሻን እንዲላመድ መደረጉ ትልቅ ለውጥ መሆኑን የተናገሩት አቶ አሻድሊ፥ ክልሉ ካለው ምቹ የእርሻ ማሳ አንፃር የኩታ ገጠም እርሻን አሁንም ማሳደግ ይገባል ነው ያሉት።
በ2017/18 የምርት ዘመን 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር ለመሸፈን ዕቅድ መያዙን አቶ አሻድሊ ገልጸዋል።
የግብርናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላትም የዘርፉን ችግሮች በመለየት እና የምርምር ስራዎችን በማጠናከር ምርታማነትን ለማሳደግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የግብርናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት እና የምርምር ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026